Home
Language
English
Türkçe
Bahasa Indonesia
About
Privacy Policy
Terms of Service
Pricing
Sign In
Download All
Share
1888 Radio
@1888Radio
Joined February 2023
1
Following
2.5K
Followers
838
Posts
Pinned Tweet
1888 Radio
@1888Radio
almost 2 years ago
"1888 የአማራ ራዲዮ ወቅታዊና ተጨባጭ መረጃዎችን ለማድረስ ድጋፋችንን ይሻልንና ኑ! አንተባበር! እንደጋገፍ! በአንድነት ፀንተን እንቁም:: " https://t.co/Dhkx6OKjQl
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ጨፍላቂው የገዳ ስርአት ሲጋለጥ https://t.co/ViBRUSbWpN via
@YouTube
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ! / ለአማራ የህልውና ትግል ፈተና የሆኑ አካላት በህዝብ እና ታሪክ ይጠየቃሉ! / ሚያዚያ 20፣ 2017 ዓ ም / ድል ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት! ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ! ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም. ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
6ኛ--- የ4ቱ አደረጃጀት መሪዎች በአደባባይ በተናገሩት መሠረት፣ በየጠቅላይ ግዛቱ አንድ አደረጃጀት ብቻ እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም እንፈጥራለን ብለው፣ ወልቃይት እና ራያን በኃይል አስመልሳለሁ ከሚለው ፅንፈኛው እና ጦረኛው የወያኔ አንጃ የፋይናንስ እና የጦር መሣሪያ ድጋፍ በመቀበል በ4ቱም ጠቅላይ ግዛቶች በአፋህድ ላይ ወታደራዊ ጥቃት መሰንዘራቸውን፣ በዚህም በጥቅሉ በአማራ፣ በተለይ ደግሞ ላለፉት 35 ዓመትት በስቃይ በኖሩት የወልቃይት እና የራያ ህዝብ ላይ ክህደት መፈፀማቸውን፣ 7ኛ--አፋህድ ከየትኛውም ወገን የሚፈፀምበትን ወታደራዊ ጥቃት የመከላከል ተፈጥሯዊ መብት እንዳለው እና አማራጭም እንደሌለው፣ 8ኛ---በ4ቱ አደረጃጀቶች መግለጫ ላይ በተጠቀሱት አውደ ውጊያዎች ሁሉ የአፋህድ ኃይሎች አስቀድመው ተኩስ ያልከፈቱ መሆናቸውን እና እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ የተንቀሳቀሱ መሆናቸውን፣ 9ኛ---አፋህድ ጦርነት ተከፍቶበት ብዙ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም፣ በ4ቱ አደረጃጀቶች በሚዲያ የሚደረጉ ስም ማጠልሸቶ እና የሚራገቡ ውሸቶች ብልጽግናን ከመርዳታቸው ባሻገር ህዝባችንን እያወዛገበ፣ የአማራን ክቡር እና ጨዋነትን እያኮሰሰ በመሆኑ፣ አደረጃጀቶቹ ወደቀልባቸው ተመልሰው ልዩነታችንን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆናችንን በህዝብ እንዲታወቅልን እንፈልጋለን። በመጨረሻም፣ በጅምላ የተጨፈጨፈውን አማራ አክብረን ልናስከብረው ይገባል። የህልውና ትግሉ የወለዳቸውን መሪዎቹን አዋርደን ልናስከብረው አንችልም። መሪዎቹ በሀሰት ተሰድበው ለሰዳቢ፣ በሀሰት ተዋርደው ለአዋራጅ እየተሰጡ ናቸው። ይህ እንዲሆን 4ቱ አደረጃጀቶች የተጫወቱት የፈር ቀዳጅነት ሚና በእጅጉ የሚያሳዝን ነው። አማራ ኃይማኖተኛ፣ ጀግና፣ሀገር ወዳድ፣ ታሪክ አክባሪ፣ ይሉኝታ ያለው መሆኑን ወዳጁም ጠላቱም ሲመሰክርለት ኖረዋል። በዚህ ልክ ያልቆመ የፋኖ አደረጃጀት ፈፅሞ ህዝባዊ ሊሆን አይችልም። ጨዋነት ለአማራ ፋኖ አማራጬ አይደለም። ተፈጥሮው ነው። ሁሉም በዚህ ልክ ለመገኘት በያለበት ይትጋ። አሁንም ግዜ አለ። ድል ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት! ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ! ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም. ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
Who to follow
🖤 Enana | እናና
@enanaye1
Human rights advocate fighting for justice, equality, and freedom for all. https://t.co/pZKLPcZ2gy
ABC TV
@AmharaBCenter
ABC TV is a not-for-profit TV station that advocates for Amhara people of Ethiopia.
Thefinalthird
@Thegoonernhisd1
Amhara born & bred. የ ሸዋ አበባ ያብባል ገና፦
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
1888, ሚያዝያ 2017 ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ! / ለአማራ የህልውና ትግል ፈተና የሆኑ አካላት በህዝብ እና ታሪክ ይጠየቃሉ! / ሚያዚያ 20፣ 2017 ዓ ም / የአማራ የኀልውና ትግል ግቡን እንዲመታ አማራዊ ድርጅትን መሠረት ማድረግ አለበት፡፡ ይህን እውነታ መሠረት አድርጎም፣ የህልውና ትግሉ ሂደት የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በራሱ ግዜ ወልዶታል፡፡ ይህም የህልውና ትግሉ የተጎናፀፈው የበሰለ የእድገት ደረጃ ነፀብራቅ ሆኗል። አፋሕድ፣ ብቸኛው የአማራ ሕዝብ ተቋማዊ የትግል ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግሉ አቅጣጫውን እንዳይስት በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በአንፃሩ፣ ትግሉን ወደኋላ በመጎተት ላይ የተጠመዱ እና እራሳቸውን "4ቱ የፋኖ አደረጃጀቶች" ብለው የሚጠሩት ኃይሎች፣ በትላንትናው ዕለት፣ ማለትም፣ ሚያዚያ 19፣ 2017 ዓ ም ባወጡት መግለጫ ፣ የድርጅታችንን ስም እንደወትሮው ጭቃ ለመቀባት ባዝነዋል ፡፡ የ4ቱ አደረጃጀቶች ጥቂት አመራሮች ያወጡት መግለጫ እንደተለመደው በሐሰት ትርክትና ፍረጃ የተሞላ ብቻ ሳይሆን፣ ከራሱ ይልቅ የሌሎች ፍላጎት ማስፈሚያ ነው፡፡ በእኛ በኩል፣ እንዲህ ዓይነት የሐሰት ፕሮፖጋንዳዎችን በአብዛኛው በዝምታ የምናልፍ ቢሆንም፣ አንዳንዴ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ምላሻችን የሰከነ፣ ጨዋ እና የተመጠነ መሆኑን የምናረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ "ያለ አማራ ድርጅት የአማራን የህልውና ትግል እንመራለን" የሚሉ ወገኖች ቆም ብለው የሚያስቡበት ልቦና እንዲሰጣቸው በጅምላ በሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ስም ፈጣሪን እንደምንለምንላቸው ሁሌም በማሳሰብ ነው፡፡ ልክ እንደ ህዝባችን፣ እኛም በፋኖ ስም የሚራገቡ የጎንዮሹን ፍትጊያዎችን አምርረን ነው የምንጠየፈው። መላው ህዝብ ከሰሞኑ ዜናዎች ጠንቅቆ እንደሚያውቀው፣ በአፋህድ ላይ ጀግናውን የህዝብ ልጅ አርበኛ ከፍያለው ደሴ እና ሌሎች አያሌ አርበኞችን የበላ ጦርነት ከተከፈተበት ሰንባብቷል። በጦር ኃይል የተመኙትን መጨበጥ የተሳናቸው የ4ቱ አደረጃጀቶች እፍኝ የማይሞሉ መሪዎች፣ በመገናኛ ብዙሃን በኩል በከፈቱት የሥነ ልቦና ጦርነት በርካታ ውሸቶችን ተናግረዋል። ለተሰነዘሩት ውሸቶች በሙሉ ምላሽ መስጠት እራሳችንን ብቻ ሳይሆን የአማራ ህዝብንም ማቅለል ስለሚሆን፣ በህልውናው ትግል ውስጥ ያሉት 9 እውነታዎች ከዚህ በታች የተሰነዘሩት ናቸው:- 1ኛ-- 4ቱ አደረጃጀቶች ከ8 ወራት በፊት፣"በሳምንታት እውን እናደርገዋለን"ብለው ቃል የገቡትን የአንድነት ድርጅት እስካሁን መመሥረት ባለመቻላቸው፣ በአጥፍቶ-መጥፋት መንፈስ ብቸኛውን የአማራ ድርጅት የሆነውን አፋህድ ለማፍረስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለህልውና ትግሉ መራዘምና መወሳሰብ ዋነኛ ምክንያት እንዳደረጋቸውና በህዝብ እና በታሪክ እንደሚጠየቁ፣ 2ኛ--- አንድ ድርጅት መመስረት ያቃታቸው በስልጣን በመጣላት እንደሆነና፣ ከዚህ በፊት በምርጫ ሲሸነፉ አፋህድን ረግጠው የወጡትም የስልጣን ጥያቄ በማንሳት እንደነበር፣ 3ኛ--- በመካከላቸው ያለው አለመግባባት ሲያበሳጫቸው እና ተስፋ ሲያስቆርጣቸው፣ "አፋህድን አፍርሳችሁ እንደ ጠቅላይ ግዛት አንድ እንሁን፣ የአማራ ድርጅት አያስፈልግም" የሚል ኋላቀር የዘመነ-መሳፍንት ቀመር ይዘው "በቀጠናዊ(በጎጣዊ) ትስስር" ስም ብቅ ማለታቸውንና፣ በእኛ በኩል፣ "በጎጣችን ስም አልተጨፈጨፍንም፣ አልተፈናቀልንም፣ አልተጨቆንም" የሚል ምላሽ የሰጠናቸው መሆኑን፣ 4ኛ-- "በየጠቅላይ ግዛቱ ከአንድ አደረጃጀት በላይ መኖር የለበትም፣ በኃይል እናጠፋቸዋለን" ብለው በተደጋጋሚ በአደባባይ የተናገሩት የ4ቱ አደረጃጀቶች መሪዎች ብቻ መሆኑን ማንኛቸውም ሰው ከማህበራዊ ሚዲያ በቀላሉ ማረጋገጥ እንደሚችል፣ ይህም የአገዛዙ አጄንዳ መሆኑን፣ 5ኛ-- በተመሳሳይ መንገድ ፣ የአፋህድ መሪዎች ሁሌም ስለ አንድነት እንደሚናገሩ ከዚያው ከማህበራዊ ሚዲያ ሁሉም ሰው ማረጋገጥ እንደሚችል፣
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
በአገዛዙ ወታደሮች በማጋስ ቀበሌ የተፈፀመው ምንድን ነው? ዝርዝር መረጃውን ከስፍራው በድምፅ አድርሰውናል:- በአንድ ሚኒባስ ተሳፋሪዎች ላይ የአገዛዙ ወታደሮች በፈፀሙት የተኩስ እሩምታ በትላንትናው ዕለት አንድ የሕክምና ዶክተርን (ዶ/ር ገብረ ሚካኤል ወልደ አማኑኤል የተባለ )ን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል። በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 16 ቀን 2017ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ ከአለም ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ልዩ ስሙ ማጋስ ቀበሌ መሳለሚያ በተባለ ቦታ መከላከያ በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ ጥዋት 2:30 በከፈተው ጥቃት የአለም ከተማ እናት ሆስፒታል ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ የሆነው ዶ/ር ገ/ሚካኤል ወ/አማኑኤል፣ የ1 ዓመት ጨቅላ ሕፃን እና ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ቁስለኞቹ በዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ላይ ሲሆኑ የሁለት ዓመት ሕፃን ጨምሮ ሌሎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ደብረብርሃን ሆስፒታል ተልከዋል። ═══════❁✿❁═══════ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLSF8
See More
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ፦ “ስለ ህዝብ የወጣ ለምን ህዝብን?” ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለአማራ ህዝብ! እውነት ታሸንፋለች! ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚያዚያ 17/2017 ዓ/ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ፦ “ስለ ህዝብ የወጣ ለምን ህዝብን?” የአማራ ፋኖ ነፍጥ አንግቦ ወደ ጫካ የገባው የአማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልው አደጋ ለመቀልበስ እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት እንደሆነ የዓለም ህዝብ ያውቃል። የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ሲባል የህይዎት፣ የዲሞክራሲ፣ የመንግስት አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የእርስትና የማንነት፣ የባህል፣ የታሪክ፣ የህገ-መንግስት፣ የስነ-ልቦና እና በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ እሴቶችን ያጠቃለለ መሆኑን ለሁላችንም ግልጽ ነው። በመሆኑም እኛ የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አባላትና አመራሮች እነዚህን የህልውና አደጋ ያለባቸውን ሁሉ የአማራን ህዝብ በሚመጥንና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ህልውናቸውን ህልው የማድረግ ዓላማን አንግበን የምንታገል፣ የምንቆስል፣ የምንሰዋ እና የምናስቀጥል ከመሆናችን ባሻገር “ህዝባችን ምን ይላል?፣ ህዝባችን ምን ይፈልጋል?” በማለት ህዝብንና ሀቅን መሰረት አድርገን የምንታገል እንደሆን የአደባባይ ሚስጢር ነው። ነገር ግን በአማራ ህዝብ የወል መጠሪያ በሆነው፣ የአይበገሬነትን ስሜት ባነገበው፣ በባርነት ከመኖር ይልቅ በነጻነት መሞትን ምርጫ ባደረገው፣ ለህዝብና ለሀገር ያለስስት የማይደራደር፣ በጥቅምና በወዳጅነት ለወጣበት የትግል ዓላማ ያለመታለል ምሳሌ በሆነው በፋኖነት ስም ከህዝብ መሰረት ውጭ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ቡዲኖችና ተላላኪዎች አማካኝነት በአማራ ህዝብ ላይ በህይዎት፣ በኢኮኖሚ፣ በዘረፋ፣ በእገታ፣ በባንክና መሰል የህዝብ ተቋማት ላይ፣ በሰብዓዊነት ጥሰት እና በመሳሰሉ የገዡን ስርዓት በማገዝ በሚመስል መልኩ በህዝባችን ላይ የተለያዩ ግፎችን ሲያደርሱ እንሰማለን፤ የውስጥ መረጃዎችም ይደርሱናል፤ ህዝባችንም ይህን እኩይ ተግባር ማን እንደሚፈጽመው ጠንቅቆ አውቆባቸዋል። በተለይ የአማራ ጠላት በሆነው ህወሀት መሩ ኢህአዴግ ልዩ በሆነ የጭካኔ ተግባሩን ሲፈጽምባት በነበረ በ2008 እና 2010 ዓ/ም፣ በኋላም የኦህዴድ መሩ ብልጽግና ባወጀው የ2013 ዓ/ም ጦርነት፣ በዚሁ የህልውና ትግል ላይ ደግሞ በህቡዕ አደረጃጀት መስዋእት በመክፈል የምትታወቀው ደም መላሿ ወልዲያና በዙሪያዋ ባሉ ህዝቦች ላይ ትግል ሳይሆን ሀብት፣ ድል ሳይሆን ዝናን፣ አንድነትን ሳይሆን መለያየትን፣ መርህ ሳይሆን ፍላጎትን መሰረት አድርገው የህዝብን ሀብትና ንብረት በመዝረፍ፣ በማፈንና በማስገደድ በተጨማሪም ከስርዓቱ አገልጋይ ባለስልጣን ጋር በመወዳወድ በአንተ ላይ እርምጃ አንወስድም ነገር ግን ገንዘብ አምጣ፤ ባለሀብትም ጠቁመን በማለት ህዝባችን መከራ እየተቀበለ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል። ህዝቡም በመማረሩ የማይገባቸውን ቅጣት እየተቀጡ መሆኑንና በተልእኮ ተቀባይ ፋኖ ነን ባዮች አማካኝነት እውነተኛውን ፋኖ ከህዝብ ለመለየት እየሰሩ እንደሆነ ህዝባችን አውቆታል። ስለሆነም እኛ የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከሌሎች የአማራ አጽመ እርስት ከሚንቀሳቀሱ አማራዊ አደረጃጀት ካላቸው የአማራ ፋኖዎች ጋር በመሆን እየታገልን ያለነው ህዝባችንን የበደለውን ስርዓት ከመደምሰስ ባሻገር ህዝባችንን በሚበዘብዝና የሚነጣጥል የትኛውንም ቡድን ከማውገዝም በተጨማሪ እንዚህን በዝባዥና ነጣጣይ ቡድኖች ከህዝባችን ጋር በመሆን የምንታገላቸው መሆኑን እየገለጽን፤ የትግል መነሻችን ህዝብ እንደመሆኑ መጠን ህዝባችንን የሚበድል ማንኛውንም እኩይ ተግባር ፈጻሚ ቡድኖችን የማንታገስ እንደመሆናችን ሁሉም የአማራ ህዝብ ይህን ተግባር የሚፈጽሙትን በጋራ እንዲንዋጋቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለአማራ ህዝብ! እውነት ታሸንፋለች! ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚያዚያ 17/2017 ዓ/ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ሻለቃ አመራሩ ገቢ ሆኗል ፡፡ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በልዩ ኦፕሬሽን ከፍተኛ የብልፅግና ወታደራዊ አዛዥ ጫኔ ለገሰ አሊ በቁጥጥር ስር ውሏል። በከፍተኛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ያለምንም መሰዋትነት ከደብረብርሀን ዙሪያ ቀይት ላይ የመከላከያ ሻለቃ አመራሩ በተዘናጋበት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የካቲት 17/2017 ዓ.ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ለፋሲካ በዓል የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት፦ መልካም የትንሳኤ በዓል ! ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለተገፋው ህዝባችን! ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚያዚያ 11/2017 ዓ.ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከፋኖ አመራሮች የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት https://t.co/hPOtMrFgCr via
@YouTube
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከ አማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የተላለፈ የትንሳኤ በዓል መልዕክት (ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም.) ምንም እንኳ የአማራ ሕዝብ ኀልውናው አደጋው ውስጥ ገብቶ፣ ከፋሽስታዊ አገዛዙ በምድርና በሰማይ በሚወርድበት እሳት እየተፈተነ ቢሆንም፣ በዚህ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ በሞትና በሕይወት መካከል ውስጥ ለሆነው ሕዝባችንና ሠራዊታችን ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በጽናት አደረሳችሁ፡፡ የአማራ ፋኖ ይፋዊ የትጥቅ ትግል የጀመረው አሁን ላለንበት የኀልውና ትግል አንደኛውና ዋና ገፉ ምክንያት፣ ብአዴንና ርዝራዦቹ የዘመናችን አስቆረቱ ይሁዳ ሆነው በሕዝባችን ላይ በፈጸሙት ክህደት፣ ሕዝባችንንም አሳልፈው የሰጡት በመሆኑ ነው፡፡ የመስዋዕት በግ ሆኖ የቀረበውን የአማራ ሕዝብ ከታወጃበት የዘር ማጥፋት ዓላማ ያለው ጦርነት በክንዳችን ለመታደግ ዛሬም በትግል ሜዳው ጸንተን ድርጅታዊ ትግል በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ርግጥ ነው ከነገው ትንሳኤ በር ለመድረስ ሰሞነ ሕማማትን ማለፍ ግድ እንደሆነው ሁሉ አማራ ወደማይቀረው ድል ከመድረሱ በፊት የመከራውን ዘመን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ ነገር ግን አንድ ዕውነት አለ፤ በፈተናው የበረታ የጨለማውን ጊዜ ያልፈዋል፤ ሕማማቱን የጸና የትንሳኤውን ብርሃን ያየዋል፡፡ ትግላችን የቱንም ያህል ፈታኝና መራራ ቢሆንም የማይተካ ሕይወታችንን ዋጋ እየከፈልን የአማራ ሕዝብን ትንሳኤ በመስዋዕትነታችን እናረጋግጠዋለን፡፡ ይህን የትግል ቃልኪዳናችንን እያስታወሰን የትንሳኤ በዓል በአብሮነት የሚከበር በዓል በመሆኑ ካለንበት ወቅታዊ የትግል ሁኔታ አኳያ በዓሉን ስናከብር በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ የደም ግብር የለመደ ፋሽስታዊው የብልጽግና አገዛዝ ከሰሞኑ በሕዝባችን ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ተከታታይ ጅምላ ጨራሽ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶች በዓሉ ዋዜማና ሰሞናት ሊቀጥል የሚችል መሆኑ ታውቆ፣ ለጥቃት ተጋላጭ ሊያደርጉን ከሚችሉ መሰባሰቦችና የተጋላጭነት ሁኔታን የሚያሳድጉ ሁነቶችን ከመፍጠር ተቆጥበን፣ በተለመደው የመረዳዳት መንፈስ እንዲከበር፣ ለሕዝባችንና ለሠራዊታችን የጥንቃቄ መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡ በመጨረሻም፡- የአማራ ሕዝብ ትግል በፈተና የተሞላ፤ መራራና ዋጋ የሚከፈልበት ነው፡፡ ነገር ግን ዋጋ የምንከፍለው ለአማራ ነጻነት፣ ለኢትዮጵያ ሐገረ-መንግሥት መጽናት ነው፡፡ ፈተናና መከራው የቱንም ያህል ቢበረታ የአማራ ድል የኢትዮጵያ አሸናፊነት አይቀሬ ነው፡፡ *** ትንሳኤ ጭለማን የመርታት የብርሃን መንገድ ነው! … ትንሳኤ ከባርነት የመውጣ ነጻነት ነው! … ትንሳኤ በዕውነት መስመር የሚገለጥ አሸናፊነት ነው! … ድል ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት! ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ሚያዚያ 11፣ 2017 ዓ.ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከ አማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ የተሰጠ አጭር የሀዘን መግለጫ የሻለቃ መንበሩ ጌታየ መስዋዕትነት____ ፋኖነት ራስን ለአማራ ህዝብ ቅዱስ መስዋዕትነት አድርጎ ማቅረብ ሲሆን በዚህ ሒደትም የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች አገዛዙን ፊት ለፊት እየተጋፈጡ ሺውን አንጋለው በክብር ለአማራ ነጻነት እየተሰው ነው። ሻለቃ መንበሩ ጌታየ የዚሁ ታሪካዊ ተጋድሎ አብሪ ኮከብና ግንባር ቀደም መሪ ከሆኑት ጀግኖች አንዱ ነበር። ሻለቃ መንበሩ ጌታየ ለህዝብ ነጻነት ሲል የሞቀ ቤቱን ትቶ፡ ከጓዶቹ ጋር ሌት ከቀን በዱር በገደሉ ሲንከራተት የነበረ ጓዳችንና መሪያችን ነበረ። ጓድ ሻለቃ መንበሩ ጌታየ ከሰሜኑ ጦርነት እስከ አሁኑ ባለው የህልውና ተጋድሎ የሰራው ጀብድ እና የመሪነት ጥበብ ልዩና አይረሴ ነበር። ጓዳችን ሻለቃ መንበሩ የመብረቁ ተፈራ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ ቀጠናው ላይ በእርሱ መሪነት ትላልቅ ጀብዶችን ሲፈጽም የቆየ ሲሆን በዚህም በሞጣ፣ በደጋዳሞት፣ በጎንጅ ቆለላ፣ በቡቡኝ፣ በሰዴ እና በደብረ ኤልያስ ... ድረስ በተባለበት ቦታ ሁሉ ጦሩን ይዞ ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ሲያደርስ የቆየ ሲሆን በዚህ ሒደትም ባስመዘገበው ድንቅ የመሪነት ጥበብ የግዙፋ የተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር ሰብሳቢ ሆኖ በዘመቻ አንድነት በሞጣ፣ በጎንጅ ቆለላ፣ በወይንውሐ፣ በቢቡኝ ድጎ ጽዮን ትላልቅ ጀብዶችን የሰራ ሲሆን ለአብነትም ቢቡኝ ድጎ ፅዮን ላይ በመራው የአንድ ቀን ኦፕሬሽን ከ96 በላይ ጠላት ደምስሶ፣ ምርኮኛና ቁስለኛውን በእያይነቱ ያደራረበ ጀግና ነበር። ደመላሹ ሻለቃ መንበሩ ጌታየ በዛሬው እለት በምስራቅ ጎጃም ሰዴ ላይ ጠላትን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ ድሉን ሊቋጭ ትንሽ ሲቀረው በመጨረሻ ሰዓት በቀረው ጥይት ራሱን ሰውቶ የአባቶቻችን ታሪክ የሰራ ልበ ሙሉ ጀግና ነው። ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLSF8
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
የወሎ ጠቅላይ ግዛት የምክክር ኮሚሽን ተሳታፊዎችን አሰረ ፣ በጎጃም 120 ንፁሀን በድሮን ተጨፈጨፉ ፣ ጭስ አባይ አካባቢ የተረሸኑ ንፁሀን ማንነት መታወቅ...https://t.co/JZjd1cweJv via
@youtube
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከዓለም አቀፍ የዐማራ ኮንግረስ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ April 15th, 2025 File 041525-001 "በአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ውስጥ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ግዙፉን ክፍለ ጦር ይመራ የነበረው፣ የገብርየ ክፍለጦር ዋና አዛዥ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተቀዳሚ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ በሕወሓት ተላላኪ "ፋኖ" ነን ባዮች በሽምግልና ስም ከበባ በመፈጸም፣ ልብ በሚሰብር ክህደት ከጀርባ ተመቶ ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም. ተሰውቷል" (ከዐማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ መግለጫ የተወሰደ) በአርበኛ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው ላይ የተፈጸመው ግድያ (assassination) ለመላው ዐማራ ህዝብ ትልቅ የልብ ስብራትን የፈጠረ ከባድ የክህደት ወንጀል ነው። በጀግናችን ሞት ዓለም-አቀፍ የዐማራ ኮንግረስ የተሰማውን መሪርና ጥልቅ ሃዘኑን ይገልፃል። አርበኛ ከፍያለው ለዓመታት የህዝቡ አለኝታና መከታ ሆኖ የጠላትን ጥቃት በጀግኘንነት ሲመክት የቆየ ወደር የለሽ የህዝብ ልጅ ነበር። ፋኖነትን የዐማራ የጀግንነት ክብር በማድረግ የትሕነግን ወረራ በጎንደር እና በወሎ በአስደናቂ ወታደራዊ ጀብዱ የመከተና የአገርን ህልውና ያስጠበቀ፣ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ የመጀመሪያውን የፋኖ ግዙፍ ክፍለጦር በመመስረት የዐማራን ትግል መልክ ያስያዘና የፋሺስቱን የብልጽግና ጦር ቅስም የሰበረ የጀግኖች ጀግና ነበር። ምን ያደርጋል! ጠላት ስንት ዋጋ ከፍሎና ደክሞ ያልተሳካለትን፣ በዐማራ ሆዳምና ቅጥረኞች ተነጠቅን። አንገት የሚያስደፋ የክህደት ድርጊት ነው!!! በአንዳንድ የተወሰኑ የፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ በጥቂት አመራር ላይ በተቀመጡ ግለሰቦች ፍላጎትና ሴራ እንዲሁም ከጠላት ኃይሎች ጋር በመተባበርና በመናበብ ስልጣንን እና ጥቅምን የሞትና የሽረት ጉዳይ አድርገው ከወጡለት ዓላማና ግብ ባፈነገጠ መልኩ ከህልውና ትግሉ በላይ ያሳሰባቸው እስኪመስል ድረስ የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ ተስኗቸው፣ በጓዶቻቸው ላይ ትንኮሳ፣ አፈና፣ እገታና ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ማድረግ ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ወደ አንድ ድርጅት ለመምጣት የማያስችል የመስመርና የአካሄድ ልዩነት ቢኖር እንኳ፣ የራስን የተማከለ አደረጃጀት በመፍጠር የህልውና ትግሉን በጋራ ተናቦ ማስቀጠልና ዳር ማድረስ ሲቻል ፣ ጉዳዩን በማክረር ወደ እርስ በእርስ መገዳደል ማድረስ እና አይተኬና እንቁ የፋኖ መሪዎችን ህይወት መቅጠፍ የተቀደሰውን እና ፍትሃዊ የሆነውን የዐማራ ህልውና ትግል ማቆሽሽና የለየለት ፀረ ዐማራነት ነው። ለእንዲህ ዓይነቱ አደገኛ አካሄድ ቶሎ መፍትሄ የማይበጅለትና ሁኔታው በዚህ መልክ የሚቀጥል ከሆነ፣ በዚህ የርስበርስ መገዳደል ተጠቃሚና አሸናፊ የሚሆነው በዋናነት በዙሪያው የከበቡትና እረፍት የነሱት የዐማራ ጠላቶች ናቸው። የተፈጠረው ቀውስ ከቁጥጥር ውጭ ከሆነና እየሰፋ ከመጣ ህዝባችን ጠላት ከሚያደርሰበት ጥፋትና እልቂት በተጨማሪ፣ ለባሰ ትርምስና ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ መዳረጉ አይቀሬ ነው። "ለፋኖ አንድነት ስንል መገደል የማይገባውን ወንድማችን ለመግደል ተገደናል" በሚል አስነዋሪ መግለጫ ግድያ መፈጸማቸውን ያመኑ የጦር አበጋዞች እንዳሉ ባደባባይ ተሰምቷል። "በአንድነት ዘመቻ" ስም አፈሙዝን በራስ ወገን ላይ ማዞርና ለመስዋትነት ማቅረብ ቃየልነት ነው። ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ሊቀመንበር ፋኖ እስከንደር ነጋን ለማሳነስ የሚደረግ ማናቸውም ጥረት ተቀባይነት የለውም ! ═══════❁✿❁═══════ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLSF8
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ (ሚያዚያ 6፣ 2017 ዓ.ም) በመስፍን ከፈለኝ የተፈፀመው ድርጊት ድርጅታዊ እውቅና የለውም!! ድል ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት! ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ሚያዚያ 6፣ 2017 ዓ.ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLSF8
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ (ሚያዚያ 6፣ 2017 ዓ.ም) በመስፍን ከፈለኝ የተፈፀመው ድርጊት ድርጅታዊ እውቅና የለውም!! የአማራ ሕዝብ ከሚደርሱበት ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋትና ማፅዳት ራሱን ለመከላከልና ለማዳን የትጥቅ ትግል ብቸኛ አማራጭ መሆኑን በመታመኑ፣ የመዳንና የመኖር ዓለማን ከግብ ለማድረስ ከ50 ዓመታት በኋላ ከደምና አጥንት የተወለደ አታጋይ ድርጅት ተመስርቷል። ሆኖም የአማራ ህዝብ ለዓላማው አታጋይ ድርጅት እንዳይኖረው በውስጥና በውጪ ሰርጎ ገቦች ሲሰራበት የኖረውን የዘመናት ሴራ፣ ዛሬም እንደወትሮው ቀጥለዋል፡፡ ትግላችን ሕዝባዊ መሠረቱ እየሰፋ፣ በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀት፣ በትግል አድማስ፣ በወታደራዊ ቁመና፣ ከአማራ ኀልውና አልፎ የኢትዮጵያን ሐገረ-መንግሥት የማስቀጠል ቁመና ላይ ደርሶ ሲያዩ፣ "ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ነች ይሏታል" እንዲሉ አበው፣ ውስጣችን አድብተው በቆዩ ሰርጎ ገብ ግለሰቦች በኩል ድርጅታችን ከብአዴን/ብልፅግና ጋር የድርድር ሂደት አንደጀመረ አስመስለው ማደናገሪያ ይዘው ብቅ ብለዋል። ይሄ ድርጊት ከጀርባው ተወግቶ ከተሰዋው የትግላችን ምልክት ከሆነው አርበኛ ከፍያለው ደሴ ግድያ ማግስት የተፈፀመ መሆኑ፣ አማራ አቀፍ የታጠቀ የፋኖ ድርጅት እንዳይኖር ወልቃይትና ራያን በጦርነት ለመያዝ የቋመጡ ፅንፈኞች እና ፋሺስቱ የብልፅግና መንግስት ምን ያህል ተናበው እንደሚሰሩ ተጨባጭ ማመላከቻ ነው። ስለሆነም:- 1. በመስፍን ከፈለኝ ስለተፈፀመው ድርጊት አፋህድ እንደ ድርጅት ምንም እንደማያውቅና እንደ ህዝቡ በማህበራዊ ሚዲያ የሰማው መሆኑን፣ 2. መስፍን ከፋለኝ በየትኛውም እርከን ካሉ የአገዛዙ ወኪሎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዲያደርግ ያልተወከለ መሆኑን፣ 3. መስፍን ከፈለኝ በድርጅታችን ሕገ-ደንብ መሰረት በህግ ቁጥጥር ውስጥ እንዲውልና፣ ሰብዓዊ መብቶቹ በተጠበቁ መልኩ ምርመራ እንዲደረግበት ትዕዛዝ መተላለፉን፣ 4. ከምርመራው ውጤት ቦኃላ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ፣ 5. የስልክ ቅጂው የተለቀቀው በአገዛዙ መሆኑን፣ 6. የአገዛዙ ዓላማ ድርድር ቢሆን ኖሮ ቅጂውን በዚህ ግዜ የሚለቅበት ምንም ምክንያት የሌለው መሆኑን፣ ድርድር እና ሰላም የሚላቸውን ለማደናገሪያነት ብቻ የሚፈልጋቸው መሆኑ በዚህ ድርጊቱ በመረጋገጡ፣ ህዝባችን የጀመረውን የትጥቅ ትግል አጥብቆ እንዲያስቀጥል አጥብቀን እናሳስባለን። ድል ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት! ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ሚያዚያ 6፣ 2017 ዓ.ም ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLSF8
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በወቅጣዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ አማራ በአማራነቱ እንዲጠፋ ስርዓታዊ መዋቅር ተዘርግቶ ዘመቻ ከተደረገበት ስድስት አስርት አመታትን አሳልፏል። ይህ እንዲሆን ከሚደረግባቸው አሰራሮች አንዱ የሆነው አማራ የራሱ የሆነ ድርጅት እንዳይጠር ከማድረግ ባሻገር ጥንቁቅና አስተዋይ መሪ እንዳይኖር በማድረግ ነው። ድርጅታዊ አሰራር አለ ሲባል የድርጅት መርህ ወይም ህግና ደንብን መከተል ማለት ነው። በዚህም መሰረት በትናንቱ እለት ማለትም ሚያዚያ 05/2017 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የ(አፋሕድ) ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት እና የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራር የሆኑት አርበኛ መስፍን ከፈለኝ ከአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ከሆኑት አቶ አብዲ ሁሴን ጋር “በስልክ ውይይት እያደረጉ ነው” ተብሎ የተለቀቀ የድምጽ ቅጅ በሚዲያ ሲዘዋወር አይተናል። በመሆኑም ምንም እንኳ ለውይይት ቀረቡ ከተባለ የድምጽ ቅጆች እንደት ሊተላለፍ ቻሉ? እውነት በዚህ ዘመን ከቴክኖሎጂ አንጻር ምን ይመስላል? የሚሉት እራሱን የቻሉ ጥያቄዎች ቢሆኑም ከዕዛችን አሰራር አንጻር በውስጣችን በተዋቀሩ ኮሚቴዎች አማካኝነት እርግጠኝነቱን እስኪያጣሩ ድረስ ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅልያ ግዛት ዕዝ በጊዜያዊነት ከስራ አስፈጻሚነት ያገድን መሆኑን እንገልጻለን። በዚህም መሰረት የአማራ ህዝብ፣ በየደረጃው ያላችሁ የዕዛችን ስራ አስፈጻሚዎች፣ የዕዛችን ሰራዊት እና መላው በውስጥም በውጭም ያላችሁ የአማራ ትግል ደጋፊዎች በሙሉ፦ 1ኛ. ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት የአማራ ህዝብ ስለ አማራ ታግሎ የማያውቅ ሆኖ ሳይሆን ወጥ የሆነ ድርጅት፣ ጠንካራ መሪ እና ሥር ነቀል ለውጥ የሚፈልጉ ኃይሎችን ለይቶ በማወቅ ጠላት የሚዲያ እና በአካልም ጭምር ዘመቻ አውጀው ትግሉን ለመጥለፍ እየተሯሯጡ እንደሆነ ሊታወቅልን ይገባል። 2ኛ. ባሳለፍናቸው ሁለት የትግል ዓመታት ብዙ ስቃይ ያስተናገድን፣ የቆሰልንበት እና ጀግና ሰራዊት እስከ አመራር ያጣንበት የትግል ጊዜ ነው። በመሆኑም የአማራን ትግል ለመጥለፍና ስሜታችን እንዲቀዘቅዝ ለማድረግ ሲባል የአርበኛ ሜ/ር ጀኔራል ከፊያለው ደሴን ህልፈት ተከትለው ጠላቶቻችን አጀንዳ ለማስቀየር የሄዱበት እርቀት እንደሆነም በመረዳት የትኛውንም አጀንዳ ላለመቀበል ሁላችንም የትግሉ ዓላማ ላይ ትኩረት እንዲናደርግ በተሰውት የአማራ ሰማእታት እና ስለ አማራ ህዝብ ስንል እንጠይቃለን። 3ኛ. የጠላት ኃይል አቅም ሳይኖረው ከህወሀት ተልዕኮ የተቀበሉ በፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ገብተው የጎንዮሽ ውጊያ ውስጥ እንድንገባ ያደረጉን ኃይሎች ቢኖሩም እነሱ ጋር ካለው የጥቅምና የስልጣን እንዲሁም የዓላማ ጽናት ይልቅ እኛ ጋር ያለው ሰፊው የአማራ ህዝብ ሰቆቃ እና የመጥፋት ዝንባሌ ተረድተን የወጣንለት ዓላማ ስለሚበልጥ ጠላት የበለጠ ለመከፋፈል የማይሰጠው አጀንዳ እንደማይኖር በመረዳት በተከታታይ በሚዲያ ዘመቻ እንዳንጠለፍ ከአደራ ጭምር መልእክታችንን እናስተላልፋለን። በመጨረሻም ከላይ የተዋቀሩት ኮሚቴዎች የደረሱበትን ምርመራ ካጠናቀቁ በኋላ ውጤቱን ለትግል ደጋፊውቻቻችን፣ለህዝባችንና ለሁሉም የሰራዊት አባላቶቻችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን። ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለተገፋው ሕዝባችን! ሚያዚያ 06/2017 የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ ስሙን በወርቅ የጻፈ የአማራ እና የኢትዮጵያ አይተኬ ልጅ ነው!! (ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም.) **** ክብር ለሰማዕቶቻችን! ድል ለአማራ ፋኖ እና ድርጅቱ አፋሕድ! ድል ለአማራ ሕዝብ! ድል ለኢትዮጰያ ሕዝብ! ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLSF8
See More
1888Radio's tweet video.
1888 Radio
@1888Radio
about 1 year ago
ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ ስሙን በወርቅ የጻፈ የአማራ እና የኢትዮጵያ አይተኬ ልጅ ነው!! (ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም.) **** የአማራ ፋኖ የትግል ምልክት የሆነው የድርጅታችን ሥራ አስፈጻሚ አመራርና የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተቀዳሚ ምክትል አዛዥ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ፣ በዓላማ ቢስ ከሃዲያን ከጀርባው ተወግቶ በመሰዋዕቱ የአማራ ፋኖ ሕዝብዊ ድርጅት (አፋሕድ) መራር ሐዘን ተሰምቶታል፡፡ የጦሩ ፊት አውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ በአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ውስጥ ከፊት መስመር የሚቀመጥ የአማራና የኢትዮጰያ አይተኬ ልጅ ነው፡፡ ቀደም ሲል አማራ ላይ በአደባባይ ዝተው ጦር ያዘመቱ የሕወሓት ታጣቂ ፅንፈኞች በጋሸና የቆፈሩትን "አይሰበሬ ምሽግ" ከደረመሱት ጀግኖች መካከል ከፊት የቆመው መሪችን አርበኛ ከፍያለው ደሴ ነበር፡፡ ብአዴን ከእነ ርዝራዡ ከጋይንት ምድር ተጠራርጎ ፈርጥጦ በነበረበት በዚያ ወቅት፣ አባት አርበኞችንና ወጣት ፋኖዎችን አስተባብሮ ሰፊውን ቀጠና ከፅንፈኞቹ የጦር ወረራ በጀግንነት የተከላከለ የቁርጥ ቀን መሪ ስለመሆኑ መላው ሕዝብ ህያው ምስክር ነው፡፡ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ወደሙሉ የትጥቅ ትግል በተቀየረበት ምዕራፍ፣ የመጀሪያውን ድል ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም. በደብረታቦር ከተማ የለኮሰውም የትግሉ ምልክት ነው፡፡ በወቅቱ የመጀመሪያውን የፋኖ ትግል በአራት አቅጣጫ መርቶ የደብረ ታቦር ከተማን ሰብሮ በመግባት፣ ወደወሎ ጋሸናና ላሊበላ ሊጓዝ የነበረውን አንድ ሙሉ የብልጽግና ክፍለ ጦር ከጥቅም ውጭ በማድረግ የትግሉን ችቦ በቀዳሚነት ለኩሶታል፡፡ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ፣ በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ውስጥ ግዙፍ ክፍለጦሮችን ከሚመሩ ቀዳሚ መሪዎቻችን አንዱ ነበር፡፡ ለአማራነት ክብር፣ ለሰማዕታት የትግል አደራና ለድርጅታዊ ትግልና ወታደራዊ ሥርዓቶች ከፍተኛ ቦታ ይሰጥ የነበረው መሪያችን ላይ የተፈጸመው ክህደት በሕዝብና በታሪክ ፍርድ የሚያሰጥ ነው፡፡ ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድ አማራ አቀፍ ድርጅት ለመመስረት የተቸገሩ የተወሰኑ ግለሰብ አመራሮች፣ ከተመሰረተው አማራ አቀፍ ድርጅታችን ጋር በቅንነት አብሮ ከመስራት፣ ወይንም አማራጭ ሃሳብ የያዘ ድርጅት ከመመስረት ይልቅ፣ ለአማራ ሕዝብ አንድያ የሆነውን ድርጅት ለማፍረስ እንቁ መሪዎቻችንና ታጋዮቻችንን ለመምታት ቃታ ስበዋል፡፡ በሚያሳፍር መልኩ ደግሞ፣ "ወልቃይት እና ራያን በኃይል እናስመልሳለን" ከሚሉ የሕወሓት ፅንፈኞች ጋር እንደሚሰሩ በአደባባይ ከመናገራቸውም ባሻገር፣ ከፅንፈኞቹ ተልዕኮ እና የጦር ቁሳቁሶች እየተቀበሉ ጦር እስከማዝመት መድረሳቸውን በአደጋ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት የወልቃይት እና ራያ ነዋሪዎች፣ እንዲሁም መላው የአማራ እና የኢትዮጰያ ሕዝብ ልብ ይበልልን። በአማራ አርበኞች አጥንትና ደም የጎመራውን የኀልውና ትግል ለአማራ ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፈው ለመስጠት እየሰሩ ያሉ ጥቂት ከሃዲያን አመራሮች በከንቱ ይባዝናሉ እንጂ፣ የአማራ ሕዝብ በደሙ የጨበጣቸውን ድሎች በፍርፋሪ አይለውጥም። የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የጦሩ ፊታውራሪ ከፍያለው ደሴ ለከፈለው ውድ የሕይወት ዋጋ መራር ሐዘኑን እየገለጠ፣ መላ ሠራዊታችን፣ ደጋፊዎቻችን እና ህዝባችን በተከታታይ ለምናስተላልፋቸው መመሪያዎች እና ትዕዛዝ በተጠንቀቅ እንዲጠብቀን እናሳስባለን። የአማራው የኀልውና ትግል ያጣው አይተኬ ጀግና አርበኛ ክፍያለው ደሴ፣ በታሪክ ማህደር ስሙን በወርቅ ቀለም የጻፈ በመሆኑ በትግል ፍሬዎቹ እና በሕዝቡ ህሊና ሕያው ሆኖ ይኖራል። አደራ ጥሎብን ስላለፈም፣ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትምና። ክብር ለሰማዕቶቻችን! ድል ለአማራ ፋኖ እና ድርጅቱ አፋሕድ! ድል ለአማራ ሕዝብ! ድል ለኢትዮጰያ ሕዝብ! ፲፰፻፹፰ሬድዮ 📻 #1888Radio #1888ሬዲዮ በ17640 kHz ዘውትር ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት https://t.co/3uCMsZLkPA
See More
Last Seen Users on Sotwe
Saso Saso
Seen from
Egypt
enamorado
Seen from
United States
BDayBabes
Seen from
France
Oreeoo_0109
Seen from
Vietnam
Wahran41
Seen from
Israel
حـ‘ـصــريـ‘ـٱٱٱﭢ مـْـْْـْآكًَُـُس ♻️🔥
Kaak-Türk
Seen from
Turkey
TURK IFSA ALEMI
Seen from
Turkey
waiifu噗噗
Seen from
Turkey
Kitten
Seen from
Turkey
Trends for you
1
Elon
Under 10K tweets
2
Paraguay
Under 10K tweets
3
SpaceX
Under 10K tweets
4
Knicks
Under 10K tweets
5
Bosnia
Under 10K tweets
6
Introducing
Under 10K tweets
7
$SPCX
Under 10K tweets
8
Canada
Under 10K tweets
9
#loveislandusa
Under 10K tweets
10
Disclosure Day
Under 10K tweets
Most Popular Users
1
Elon Musk
@elonmusk
240.2M followers
2
Barack Obama
@barackobama
119.3M followers
3
Donald J. Trump
@realdonaldtrump
111.6M followers
4
Cristiano Ronaldo
@cristiano
109.4M followers
5
Narendra Modi
@narendramodi
106.9M followers
6
Rihanna
@rihanna
97.4M followers
7
NASA
@nasa
92.1M followers
8
Justin Bieber
@justinbieber
90.7M followers
9
KATY PERRY
@katyperry
87M followers
10
Taylor Swift
@taylorswift13
80.9M followers
11
Lady Gaga
@ladygaga
72.4M followers
12
Kim Kardashian
@kimkardashian
69.5M followers
13
Virat Kohli
@imvkohli
68.9M followers
14
YouTube
@youtube
68.6M followers
15
Bill Gates
@billgates
63.5M followers
16
The Ellen Show
@theellenshow
62.5M followers
17
CNN
@cnn
61.9M followers
18
Neymar Jr
@neymarjr
61.5M followers
19
X
@x
60.9M followers
20
Selena Gomez
@selenagomez
60.1M followers
Olivia
Online
✨
⭐
💫